No media source currently available
ኬንያዊያን ትናንት ሲሰጡ የዋሉት ድምፃቸው እየተቆጠረ ነው። የኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ባለስልጣን(ኢጋድ) ያሠማራውን የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በመምራት እዚያው ኬንያ ይገኛሉ ። ኢጋድ ዶ/ር ሙላቱን ታዛቢዎች ቡድኑ መሪ አድርጎ መሰየሙን ያስታወቀው ባለፈው ወር ሲሆን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርፕሮፌሰር መረራ ጉዲናም ከታዛቢዎች መካከል ናቸው።