የኢትዮጵያ መንግሥት "ሸኔ" ብሎ የሚጠራውንና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን 3 ሺሕ 180 አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግሥት አስታወቀ። እጃቸውን ባልሰጡት ላይ ደግሞ እርምጃ መወሰዱን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የታጣቂ ቡድኑ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ እርምጃ እንዲወሰድ የወሰነው ሰሞኑን ስብሰብ ኣያካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ደቡብ እዝ ምክትል አዛዥ ሞያሌ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድተዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዓለም ዓቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ኦዳ ተርቢ መንግሥት በአመራሮቻቸው ላይ እርምጃ ለመውሰድ ማቀዱን እንደሚያውቁ ገልፀው ፤ ሙከራ ከመደረጉ ውጪ የተያዘባቸውም ሆነ እርምጃ የተወሰደበት አመራር እንደሌለ ተናግረዋል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/