በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንድ እና ፓኪስታን ዲፕሎማቶች በአፍጋኒስታን የታሰረ ጋዜጠኛ ለማዳን ግፊት እያደረጉ ነው


የታሊባን ተዋጊ የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል-ዛዋሪ በተገደለበት እና ጋዜጠኞች እንዳይሄዱበት ከተከለከለበት ስፍራ ቆሞ ይታያል
የታሊባን ተዋጊ የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል-ዛዋሪ በተገደለበት እና ጋዜጠኞች እንዳይሄዱበት ከተከለከለበት ስፍራ ቆሞ ይታያል

በካቡል የሚገኙ የህንድ እና የፓኪስታን ዲፕሎማቶች በአፍጋኒስታን በእስር የሚገኘው የውጪ ጋዜጠኛ እንዲፈታ መጠየቃቸውን ተከትሎ አፍጋኒስታንን የሚያስተዳድረው ታሊባንን ግራ ተጋብቷል።

ፓኪስታናዊው ጋዜጠኛ አናስ ማሊክ ከአፍጋኒስታዊ ረዳቱ እና ሹፌሩ ጋር ሐሙስ እለት በታሊባን በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ ከፍተኛ ምርመራ እና ድብደባ ተፈፅሞበታል ተብሏል። ለ21 ሰዓታት በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ ዛሬ ከእስር መለቀቁም ታውቋል።

ሆኖም የማሊክ መጥፋት ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ የፓኪስታን እና የህንድ ዲፕሎማቶች እኩል የታሊባንን ባለስልጣናት ቀርበው ጋዜጠኛው እንዲፈታ መጠየቃቸው ታሊባኖችን እንዳስገረማቸው የአሜሪካ ድምፅ ምንጮች ተናግረዋል። "ማሊክ ፓኪስታናዊ ሆኖ እንዴት እንዲፈታ ትጠይቃላችሁ" ሲሉ የህንድ ዲፕሎማቶችን መጠየቃቸውም ተነግሯል።

ነዋሪነቱ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ የሆነው ማሊክ፣ ዋና ማሰራጫ ጣቢያው በህንድ ዋና ከተማ ለሆነ አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ የሚሰራ ሲሆን በሰላም ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የህንድ እና የፓኪስታን ኤምባሲዎች ጥረት እያደረጉ ነው።

ፓኪስታን እና ህንድ በአፍጋኒስታን የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ልዑካንን በመጠቀም በየሀገራቸው ውስጥ ዐመፅ ለማስነሳት ይጥራሉ በማለት በተደጋጋሚ እርስ በእርሳቸው የሚወነጃጀሉ መሆኑ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG