በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች በዘጠኝ ዓመት እስራት ተቀጣች


አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብርትኒ ጋይነርን ሞስኮ ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ከመሰማቱ በፊት /ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም
አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብርትኒ ጋይነርን ሞስኮ ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ከመሰማቱ በፊት /ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም

የሚጨስ የሃሺስ ዘይት ወደ ሩሲያ ይዛ ግብታለች በሚል በእስር ላይ የቆየችው ች የሩሳያ ፍ/ቤት ዛሬ ማምሻውን በዘጠኝ ዓመት እስራት ቀጥቷታል። የሃገሪቱ ከሳሽ አቃቤ ሕግ ጋይነር በዘጠኝ ዓመት ተኩል እስራት እና በ16,590 ዶላር የገንዘብ ክፍያ እንድትቀጣ ያቀረበው የቅጣት ማክበጃ በዳኛው ተቀባይነት አግኝቶ ፀድቋል።

ብሪትኒ ጋይነር ሆን ብላ ወንጀል የመፈጸም ሐሳብ እንዳልነበራት ለዳኛው አቤት አቅርባ ነበር።
ጋይነር አክላም የሃሺስ ዘይትን ውጋቷን ለማስታመም ትጠቀም እንደነበር ተናግራለች። የፈጸመችውም ስህተት ሆን ብላ እንዳልናበርና ዳኛውም የሚሰጡት ብይን ህይወቷን የሚገታ እንደማይሆን ተስፋ አድርጋለች።

ለህክምና እንዲሁም ለመዝናናት ሃሺሽ ወይም ካናቢስ እና ውጤቶቹን በአብዛኛው የአሜሪካ ግዛቶች ህጋዊ ሲሆን፤ በሩሲያ ግን በማንኛውም መልኩ መጠቀም የተከለከለ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን "ቅጣቱ ተቀባይነት የሌለው ነው" ብለዋል። ባይደን ጋይነርን ለማስለቀቅ ከሩሲያ ጋር የእስረኛ ልውውጥ እንዲደረግ ባለስልጣናትን አዘዋል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ባለፈው ሳምንት የእስረኞችን ልውውጥ በተመለከተ ተወያይተዋል። የብርትኒ ጉዳይ ሂደት ላይ በመሆኑ ግን ውሳኔ ላይ አልደረሱም።

ጠዋት በነበረው ሂደት ብርትኒ በብረት አጥር ውስጥ ሆና ሂደቱን ስትከታተል ከሩሲያ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ጋር የተነሳችውን ፎቶ ይዛ ነበር። ለክለብ አባላቷ፣ ለደጋፊዎቿ፣ ለወላጆቿ፣ ወንድምና እህቶቿ፣ እንዲሁም ለሌሎች ለፈጸመችው ስህተት ይቅርታ ጠይቃለች።

XS
SM
MD
LG