ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ደፋሪዎች ፍርድ ፊት ቀረቡደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለፈው ሣምንት ስምንት ሴቶች ላይ ከተፈፀመ በደቦ የመድፈር ጥቃት ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሰማንያ ወንዶች የፍርድ ሂደት ትናንት፣ ሰኞ ተጀምሯል።
ፊታቸውን በጭንብል የሸፈኑና መሣሪያ የታጠቁት ወንዶች ጥቃቱን ያደረሱት ሴቶቹ የሙዚቃ ቪዲዮ ቀረፃ ላይ ሳሉ እንደነበረ ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካ የመድፈርና ሌላም ፆታዊ ጥቃት በስፋት የሚፈፀምባት ሃገር ብትሆንም በስምንቱ ሴቶች ላይ የደረሰው ግን ህዝቡን እጅግ እንዳስደነገጠ ተዘግቧል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ