በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ደብረፅዮን ለፌዴራሉ መንግሥት ደብዳቤ ላኩ


ዶ/ር ደብረፅዮን ለፌዴራሉ መንግሥት ደብዳቤ ላኩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመርና የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ተወካይ አኔት ዊበር ወደ መቀሌ ሄደው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልና ባለሥልጣናት ጋራ መወያየታቸውን ልዑካኑ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በጦርነቱ ወቅት ክልሉ ውስጥ ተፈፅመዋል የተባሉ የመብቶች ጥሰቶችን ባለሥልጣናቱ ለልዑካኑ ማስረዳታቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

የዩናይትድ ስቴትስና የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ባለው ህወሓት መካከል ውይይት እንዲጀመር ለማበረታታት የጀመሩትን ተዕእኮ መቀለ ላይ የጀመሩ ሲሆን ወገኖቹ ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውንና በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው ንግግር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ አወድሰዋል።

የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ድርድሩን በተመለከተ ድርጅታቸው ያለውን አቋምና ‘አሉብን’ የሚሏቸውን ችግሮች፣ የምዕራብ ትግራይን ሁኔታ በተመለከተም ለልዑካን ቡድኑ ማስረዳታቸውን ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

ልዑካኑ ያወጡት መግለጫ አያይዞ በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የባንክና ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ መጀመር እንዳለባቸው እንደሚያምኑና በጉዳዩ ላይም ቀደም ሲል ከፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን ገልጿል።

ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዓለምአቀፍ ልዑካኑ በኩል ለፌደራሉ መንግሥት የሚሰጥ ደብዳቤ መስጠታቸውን የገለፀው የጋራ መግለጫ ደብዳቤው መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለመመለስ ለሚሠማሩ ሠራተኞች የደኅንነት ዋስትና የሚሰጥና አገልግሎቶቹን ለመመለስ ምንም እንቅፋት እንደማይገጥም የሚያረጋግጥ መሆኑን አመልክቷል።

በተመሳሳይ በግጭቱ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው የትግራይ፣ የአፋርና የአማራ ክልሎች አካባቢዎች ያልተቆራረጠ ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ በጥሬ ገንዘብ፣ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ላይ የተጣለው እገዳም እንዲነሳ ጠይቋል።

ብሄራዊ ዕርቅ እንዲኖር ተጠያቂነት ቁልፍ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች የባለሞያዎች ኮሚሽን ግጭት ወደ ተካሄደባቸው አካባቢዎች መግባት እንዲችልና ተዓማኒነት ያለው ምርመራ እንዲያደርግ ልዑካኑ ማሳሰባቸውን፣ በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም አካላት ከማንኛውም የጥላቻ ንግግርና አነሳሽ ትርክቶች እንዲታቀቡ መማፀናቸውን አብራርቷል።

XS
SM
MD
LG