በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎዳና ህይወትን አልፎ ለአሜሪካ ምክርቤት ምርጫ የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ


የጎዳና ህይወትን አልፎ ለአሜሪካ ምክርቤት ምርጫ የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

እ.አ.አ በ2022 መገባደጃ ለሚካሄደው የአሜሪካ ምክርቤት ምርጫ ከሚወዳደሩ መካከል በቨርጂንያ ክፍለ ግዛት በአርሊንግተን፣ አሌክዛንድሪያ አና ደቡብ ፌርፋክስ የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቴዲ ፍቅሬ አንዱ ነው። የቴክኖሎጂ ባለሙያው ቴዲ ከሰባት አመት በፊት ስራውን በማጣቱ ለሁለት አመት ተኩል በጎዳና ላይ የኖረ ሲሆን ያ ጊዜ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነት እንዲመለከት እና ለምክር ቤት ምርጫ እንዲወዳደር እንደገፋፋው ገልጿል።

እ.አ.አ በ2022 መገባደጃ ህዳር ወር ላይ ለሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት እና አካባቢ ምርጫ ከሚወዳደሩ ተፎካካሪዎች መካከል በቨርጂንያ ክፍለ ግዛት የሚገኙትን አርሊንግተን፣ አሌክዛንድሪያ አና ደቡባዊውን የፌርፋክስ አካባቢ ወክሎ የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቴዲ ፍቅሬ አንዱ ነው። እንደ ቦዝ አለን የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎች በቴክኖሎጂ ባለሙያነት ያገለገለው ቴዲ ከሰባት አመት በፊት ስራውን በማጣቱ ለሁለት አመት ተኩል በጎዳና ላይ ለመኖር ተገዶ የነበረ ሲሆን ያ ወቅት በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነት እንዲመለከት እና ለምክር ቤት ምርጫ እንዲወዳደር እንደገፋፋው ገልጿል።

XS
SM
MD
LG