No media source currently available
በደቡብ ክልል በክልል ለመደራጀት የጠየቁ ዞኖች መንግስት በኩታ ገጠም ወይም በክላስተር እንዲደራጁ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምፅ አፀደቁ። ሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በራሳቸው ከተደራጁ በኋላ የተቀረው የደቡብ ክልል አባል የነበሩ 11 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች በሁለት አዳዲስ ክልሎች ይደራጃሉ ተብሏል። አደረጃጀቱን በተመለከተ ውሳኔ ህዝብ ይደረግ አይደርግ የተገለፀ ነገር የለም።