በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ምክኒያት ከእርሻ ሥራቸው መስተጓጎላቸውን ገለፁ


በኦሮምያ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ምክኒያት ከእርሻ ሥራቸው መስተጓጎላቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:28 0:00

በኦሮምያ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው እና ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት ዞኖች ውስጥ አርሶ አደሮች በፀጥታ ችግር ምክኒያት ከእርሻ ሥራቸው መስተጓጎላቸውን ገለፁ።

ከምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች በፀጥታው ችግር ለምርት የሚኾናቸውን ዘር ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

የኦሮምያ ክልል ቃል አቀባይአቶ ኃይሉ አዱኛ ፤ ለአርሶ አደሮች የሚጓጓዝ የግብርና ግብዓት “ሸኔ” ባሏቸው ታጣቂዎች እንደሚዘረፍ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የሚናገሩት ኦዳ ተረቢ በበኩላቸው በመንግሥት የሚቀርብባቸውን ውንጀላ እንደማይቀበሉ ገለፀዋል።

XS
SM
MD
LG