በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኑሮ ውድነት ክንዱን ያበረታባቸው ጡረተኞች


የኑሮ ውድነት ክንዱን ያበረታባቸው ጡረተኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ የሚገኘው የዋጋ ግሽበት 34 ከመቶ የደረሰ ሲሆን ለግሽበቱ ትልቅ ሚና ያለው የምግብ ዋጋ ጭማሪ 38 ከመቶ መሆኑን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ አስታውቋል። በየግዜው እያሻቀበ የሚሄድ የኑሮ ውድነት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረ ቢሆንም በተለይ ደግሞ በመንግስት የጡረታ ገቢ የሚተዳደሩ አረጋውያን የሚከፈላቸው ገንዘብ እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ ኑሮን መቋቋም የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ይገልፃሉ።

አቶ ስለሺ ወጋየሁ ከ24 አመት በፊት ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት በማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ 40 አመታትአገልግለዋል። በወቅቱ 2ሺህ ብር ደሞዝ ያገኙ የነበረ ሲሆን ጡረታ ሲወጡ ገቢያቸው ወደ 600 ብር ገደማ ዝቅ አለ።ከጥቂት አመታት በፊት መንግስት ያደረገውን የጡረታ ማሻሻያ ተከትሎ አቶ ስለሺ አሁን በወር የሚያገኙት የጡረታገንዘብ ወደ 2ሺህ 300 ብር ከፍ ቢልም፣ አሁን ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ሲነፃፀር የሚያገኙት ገቢ የትኛውም የኑሮቀዳዳቸውን አይሸፍንም።

በ55 አመታቸው ጡረታ እንደወጡ የሚገልፁት አቶ ስለሺ አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት መቋቋም የቻሉት በግልተቋማት ሰርተው በሚያገኙት እና በልጆቻቸው ድጋፍ መሆኑን ይገልፃሉ።

የአውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ባለሙያ የሆኑት እና ለረጅም አመታት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በመንግስት እርሻ እንዲሁምበመንገድ ትራንስፖርት አገልግለው ከሁለት አመት በፊት ጡረታ የወጡት ወይዘሮ ትእግስት አሰጋኸኝ ደግሞ በጡረታየሚያገኙት ገንዘብ 2ሺህ 900 ብር ነው። በግል እና በመንግስት ዩንቨርስቲ ልጆቻቸውን ለሚያስተምሩት ወይዘሮ ትእግስትየጡረታ ገቢያቸው መተዳደሪያ ሊሆናቸው እንዳልቻለ ይገልፃሉ።

ወይዘሮ ትእግስት በወር የሚያገኙት 2ሺህ 900 ብር የወር አስቤዛቸውን እንኳን አሟልቶ አይገዛም። ይሁን እንጂ ልክእንደእሳቸው በመንግስት መስሪያቤቶች ለአመታት አገልግለው ከሳቸው ባነሰ እጅግ ዝቅተኛ ገቢ ብቻ ያለእርዳታ መኖርየከበዳቸው የመንግስት ጡረቶች መኖራቸውን በሀዘኔታ ያስረዳሉ።

በባህር ዳር ከተማ ፋሲሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ38 አመታት የሰውነት ማግልመሻ መምህር የነበሩት እና ከሶስትአመት በፊት ጡረታ የወጡት የ62 አመት አዛውንት አቶ እንዳለው ጥላሁንም እንዲሁ የሚይገኙት 4ሺህ ብር የጡረታደሞዝ የቤት እመቤት የሆኑ ባለቤታቸውን እና አራት ልጆቻቸውን በኪራይ ቤት ለማስተዳደር የማይችል በመሆኑ በውጭየሚኖሩ ወዳጆቻቸውን እጅ ለማየት መገደዳቸውን ይገልፃሉ።

አቶ እንዳለው በዚህ እድሜያቸው የሰው እጅ ማየታቸው ይክፋቸው እንጂ በተለይ በመንግስት ፋብሪካዎች ውስጥ ይሰሩየነበሩ እና አሁን ከሶስት መቶ ብር ባነሰ የጡረታ ገቢ የሚተዳደሩ ጓደኞቻቸውን ሲያዩ የበለጠ ያዝናሉ።

ይህ ደግሞ ሌላው የበርካታ ጡረተኛ አረጋውያን ችግር ነው። በብዙ መከራ ውስጥ አሳድገውና አስተምረው፣ ለቁምነገርሲበቁ ይጦሩኛል ያሏቸው ልጆቻቸው ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ ማግኘት ባለመቻላቸው ተመልሰውየጡረተኛ ወላጆቻቸውን እጅ ጠባቂ መሆናቸው የበርካታ ወላጆችን ልብ ይሰብራል፣ ተስፋም ያስቆርጣቸዋል።

ለአመታት በሙያቸው አገልግለውና በርካታ የኑሮ ውጣ ውረድን አሳልፈው ማረፍ እና በልጆቻቸው መጦር ይመኙ የነበሩበርካታ አረጋውያን በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ የሚታየው አለመረጋጋት፣ ግጭት፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የኢኮኖሚ መዋዠቅባስከተለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ያተመኙትን ኑሮ ሳያገኙ፣ በምትኩ ኑሮን መቋቋም አቅቷቸው ለከፍተኛ ድህነት እናየጤና መጓደል መዳረጋቸውን ይገልፃሉ። መንግስትና የሚመለከተው አካል ችግራቸውን አይቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸውምጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG