በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላም ውይይቱ ያለ ቅድመ ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ


የሰላም ውይይቱ ያለ ቅድመ ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:54 0:00

ከህወሓት ጋር ለማካሄድ የታሰበውን የሰላም ውይይት በየትኛውም ጊዜና ቦታ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል ። ይሄም ሆኖ መንግሥት ቅድመ ሁኔታዎችን እንደማይቀበል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጠቁመዋል።

ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከሰላም ውይይቱ በፊት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል ።

በተያያዘ ዜና የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኒቴ ዌበር ትናንት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር ባሕርዳር ከተማ ተገናኝተው ተወያይተዋል ።

የኢትዮጵያ እና የአማራ ክልል መንግሥታት የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት በድርድር ለመፍታት መዘጋጀታቸው እንዳበረታታቸው ልዩ መልዕክተኛዋ ተናግረዋል።

ህወሓት በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ፈፀማቸው ያሏቸውን ጭፍጨፋዎች እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የጠቀሱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል፤ ይሄም ሆኖ ለመነጋገር፣ ለመደራደር እና ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

XS
SM
MD
LG