በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕላቲነም የተሰኘ ጥንታዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ረድኤት ወንድሙ


ፕላቲነም የተሰኘ ጥንታዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ረድኤት ወንድሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:15 0:00

ፕላቲነም የተሰኘ ጥንታዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ረድኤት ወንድሙ

አስመራ ተወልዳ ኢትዮጵያ ያደገችው ረድኤት ወንድሙ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ሳለች ከሰባት እህትና ወንድሞቿ ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመሄድ በቺካጎ ግዛት አድጋለች። የፎቶግራፍ ጥበብ የልጅነት ህልሟ ቢሆንም በዙሪያዋ ባሉ ሰዎች ጫና ነርሲንግ ተምራለች። ይሁን እንጂ በዛ ሙያ ላይ ከዚህ በላይ ለመቆየት ባለመፈለጌ ከጊዜ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ፊቴን ወደ ፎቶግራፍ ጥበብ አዞርኩ ትላለች።

ረድኤት የመረጠች የፎቶግራፍ ዘርፍ ፕላቲነም በተሰኘ የፎቶግራፍ እጥበት እና ሕትመት ሂደት ሲሆን፤ እ.ኤ.አ 1873 ተጀምሮ ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ የተቋረጠ ነው። ረድኤት ወንድሙ የሴቶች ማንነት ውበት እና አካላት በሚያሳዩ ፎቶግራፎች ላይ ለአመታት የሚዝለቅ ስብስብ እየከተበች ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት ያሉ በከፍተኛ የስነውበት ባለሞያ የተዋቡ እና በፎቶ ሾፕ የተስተካከሉ ፎቶግራፎች እንደ ባለሞያ እውነተኛውን የሴቷን ማንነት ያሳያሉ ብላ እንደማታምን ትናገራለች።

በዋናነት ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ለመኖር ብታስብም የመረጠችው የፕላቲነም የፎቶግራፍ ህትመት ዘርፍን የሚያበረታታ እና ፎቶዎቹን ለማጠብ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ ባለመኖራቸው መመላለሱ ግድ ብሏታል። በዩናይትድ ስቴትስ ከሌሎች ልክ እንደሷው ፕላቲነም በተሰኘው የፎቶግራፍ ጥበብ ዘርፍ ውስጥ ካሉ ባለሞያዎች ጋር የፎቶግራፍ አውደ-ርዕዮችን እና ልምምዶችን ታዘጋጃለች።

ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለትም ከቡድኑ ጋር በመሆን በሜሪላንድ ግዛት ሞንጎሞሪ ካውንቲ ግሌን ኤኮ በተሰኘ ፓርክ ውስጥ ያሰናዳችው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ላይ ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርጋለች።

https://www.simplyred8.com/

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG