በኬንያ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት የጥላቻ ንግግር በዝቷል ሲል አንድ አሜሪካዊ የሰብዓዊ ድርጅት አስታወቀ።
ኬንያ በነሐሴ 3 ለማካሄድ ቀጠሮ ከያዘችለት በፊት ባሉት በነዚህ ቀናት የጥላቻ ንግግር እየጨመረ በመምጣት ላይ ሲገኝ፣ በአሜሪካ መሰረቱን ባደረገውና እንደ ሜርሲ ኮር ያሉ የሰብዓዊ ድርጅቶች የጥላቻ ንግግሩን ለመቀልበስና የፈጠራ ወሬዎችን አደገኛነትን በተመለከተ ግንዛቤን ለማሳደግ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።