በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሮምያ ክልል “ሸኔ” ብሎ በጠራው ታጣቂ ቡድን ላይ ከፍተኛ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ


ኦሮምያ ክልል “ሸኔ” ብሎ በጠራው ታጣቂ ቡድን ላይ ከፍተኛ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

የኦሮምያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መንግሥት በአሸባሪነት በፈረጀውና “ሸኔ” ብሎ በጠራው ራሳቸውን ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂ ቡድን ላይ “ከፍተኛ” ያሉት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀውና “ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ራሳቸውን ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው የሚጠሩት ታጣቂ ቡድኖች በኦሮምያ ክልል በሚኖሩ በተለይ የአማራ ተወላጆች እና ሌሎች ላይ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ እንደፈፀሙባቸው ከጥቃቱ የተረፉ መናገራቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት “ጨፌ ኦሮምያ” በሚል የሚታወቀው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሁለት ተወካዮች በክልሉ በታጣቂዎቹ እየተገደሉ ያሉት የአማራ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ የኦሮሞ ተወላጆችም ጭምር መሆናቸውን በመግለፅ መንግሥት በክልሉ እየታየ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸው ይታወሳል።

መንግሥት ከዚህ “ሸኔ” ሲል ከጠራው ታጣቂ ቡድኑ ጋራ ለመደራደር ዝግጁ አለመሆኑን የገለፁት፤ የኦሮምያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ከክልሉ ሕዝብ ጋራ በመቀናጀት እየተወሰደ ባለው እርምጃ የተሻለ ውጤት እየታየ መሆኑኑ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አለማቀፍ ቃለ አቀባይ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ኦዳ ተርቢ ግን የኦሮምያ ክልል የሰጠውን መግለጫ አጣጥለው ታጣቂ ቡድኑ ድል እየቀናው ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG