በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሺሪላንካ አዲስ ፕሬዚዳንት ሰየመች


የሺሪላንካን ባንዲራ የያዘ ግለሰብ
የሺሪላንካን ባንዲራ የያዘ ግለሰብ

የሺሪላንካ ፓርላማ ቀድሞ ለስድስት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉትን ራኒል ዊክሬሜሲኒግሄን መርጧል።

የ73 ዓመቱ ነባር ፖለቲከኛ 225 መቀመጫ ባለው ምክር ቤት የተመረጡት በድብቅ በተሰጠ ድምፅ 134ቱን አግኝተው ነው።

ምርጫው የተካሄደው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውሱን ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ውስጥ የቀደሙት ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራያፓክሳ አገር ጥለው ከወጡ ከአንድ ሣምንት በኋላ መሆኑ ነው።

ይሁን እንጂ “ዊክሬሜሲኒግሄም ለራያፓክሳ ቤተሰብ ቅርበት አላቸው” በሚል እርሳቸውም ሥልጣን እንዲለቅቁ ተቃዋሚዎች እየጠየቁ መሆኑ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG