በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታስረው የሚገኙ የኦነግ አመራር አባላት እንዲለቀቁ ታዘዘ


ታስረው የሚገኙ የኦነግ አመራር አባላት እንዲለቀቁ ታዘዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:40 0:00

በቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እሥራት ላይ ከሚገኙት ሰባት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አባላት አራቱ እንዲለቀቁ የቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው አቶ ደምሴ ፍቃዱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በተለያዩ የአመራር ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ሰባት ግለሰቦች በቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው እንደሚገኙ የተናገሩት የተከሳሾች ጠበቃ አቶ ደምሴ ፍቃዱ ከእነዚህ ውስጥ አራቱ አካልን ነፃ የማውጣት አቤቱታ አቅርበው እንደነበር አስታውሰዋል።

አቤቱታው የቀረበለት የቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት ግለሰቦቹ በማንና ለምን እንደታሠሩ የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽን ቀርቦ እንዲያስረዳ በሦስት ተከታታይ ችሎቶች ጥሪ ቢያደርግም ፖሊስም ሆነ እስረኞቹ ሳይቀርቡ መቅረታቸውን አቶ ደምሴ ተናግረዋል።

ሆኖም አርብ ሐምሌ 8/2014 ዓ.ም የኦሮምያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቀርቦ ስለ ግለሰቦቹ ማብራሪያ መስጠቱን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG