ቁጥጥሩ የጠበቀው የፌዴራል የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። ከዛሬ ሐምሌ 11/2014 ዓ.ም ጀምሮም ባለ ሁለት ጎማ ሞተር ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት ዕላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።
የ“ጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን” የሚሉ ቡድኖች በህቡዕ ስለመደራጀታቸው መረጃ እንዳለው ጠቅሶ መግለጫ ያወጣው የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በበኩሉ “የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዳያገኙ የአመፅና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ መንግሥት እርምጃ ይወሰዳል” ሲል አሳስቧል።