በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለተሰንበት ለኢትዮጵያ ወርቅ አሸነፈች


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዩጂን - ኦሬገን ላይ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በሴቶች የአስር ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዩጂን - ኦሬገን ላይ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በሴቶች የአስር ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዩጂን - ኦሬገን ላይ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በሴቶች አሥር ሺህ ሜትር የተሰለፈችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ዛሬ አሸንፋለች።

በኢትዮጵያውያን፣ በኬንያዊያንና በትውልደ ኢትዮጵያዪቱ ኔዘርላንዳዊት አትሌት ሲፋን ሀሰን መካከል ብርቱ ትንቅንቅ በታየበት በዚህ ውድድር የአምስት ሺህ ሜትርና የአሥር ሺህ ሜትር ርቀቶች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ለተሰንበት ኬኒያዊያን ተፎካካሪዎቿን ቀድማ ነው ድል የተጎናፀፈችው።

ለተሰንበት ሁለተኛና ሦስተኛ የወጡትን ብርቱዎቹን ኬንያውያን አትሌቶች አስከትላ የገባችው አሥሩን ኪሎሜርት በ 30 ደቂቃ 9 ሰከንድ 94 መቶኛ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ነው።

ዶሃ - ካታር ላይ ባለፈው ዓመት በተካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛ ሆና የጨረሰችው ለተሰንበት በሻምፒዮናው የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያዋን ማሸንፏ ነው።

አትሌቷ በቶኪዮው ኦሊምፒክ በአሥር ሺህ ሜትር ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበረች።

XS
SM
MD
LG