በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 592 ሚሊየን ዶላር ሰጠች


ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 592 ሚሊየን ዶላር ሰጠች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:12 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 592 ሚሊየን ዶላር መስጠቷን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የሥነ-ሕዝብ፣ ስደትና ፍልሰት ጉዳዮች ምክትል ሚኒስቴር ጁሊየታ ቫልስ ኖይስ በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ተገኝተው እንዳስታወቁት እርዳታው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እና በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤይድ) በኩል የሚደርስ ይሆናል።

ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው የ592 ሚሊየን ዶላር ርዳታ በዋናነት በመላው አፍሪካ ለሚገኙ ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ህይወት አድን ድጋፍ ለማድረግ የሚውል ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ እና በሳህል በሚካሄዱ ግጭቶች ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ ርዳታንም ያጠቃልላል።

ይህ ርዳታ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋማት በመላው አፍሪካ ተጠልለው የሚገኙ ከሰባት ሚሊየን በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንዲሁም ከ25 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመርዳት እንደሚያስችላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር የሆነውን 1.5 ሚሊየን ስደተኞች በማስጠለል ዩጋንዳ ቀዳሚ መሆኗን ያስታወሰው መግለጫ ከተሰጠው ርዳታ 82 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በዩጋንዳ ሰብዓዊ ርዳታ መስጫ የሚውል መሆኑን ግለጿል።

ከ41 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ተቋም የሚሰጥ ሲሆን ወደ 20 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋው ደግሞ በጤና፣ በትምህርት፣ ጥበቃ እና ገቢ አምጪ እንቅስቃሴዎችን ለሚደግፉ ፕሮግራሞች የሚውል ይሆናል።

በተለይ ጥሬ እቃዎችን ከዩክሬን እና ከራሽያ ያስገቡ በነበሩ ሀገሮች የሚኖሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች አህጉሪቱን እየጎዳ ለሚገኘው የምግብ እጥረት የተጋለጡ መሆናቸውን የገለፀው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ ዓለም በአፍሪካ ለሚታየው ሰብዓዊ ችግር የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን አሜሪካንን እንደሚያሳስባት አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG