በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡርጂ ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰዎች ተገደሉ


ደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ የታጠቁ ቡድኖች አደረሱት በተባለ ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸውን እና አምስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ገለፁ።

የወረዳው መንግሥት ኮምኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረወልድ ሂዶ ከተገደሉ እና ከቆሰሉ አርሶ አደሮች በተጨማሪ ከ50 በላይ ከብቶች መዘረፋቸውን አስታውቀዋል። በጥቃቱም ሱሮ ባርጉዳ መሽገዋል ያሏቸውን ታጣቂ ቡድን ወንጀለዋል።

በተመሳሳይ ታጣቂ ቡድን በአማሮ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት አንድ አርሶ አደር መገደሉን የአማሮ ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ታጣቂ ቡድኑ ይንቀሳቀስባቸዋል ከተባለው ኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት የኦሮሞ ነፃነት ጦር ወይም ሠራዊት ቃል አቀባይ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ኦዳ ተርቢ ከዚህ ቀደም በዚህ አካባቢ ስለሚደርሰው ጥቃት ተጠይቀው ውንጀላውን ማስተባበላቸው ይታወሳል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ቡርጂ ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00

XS
SM
MD
LG