በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመጠጥ ቤት ታዳሚዎች ላይ በተከፈተ የእሩምታ ተኩስ  19 ሰዎች ተገደሉ


.
.

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ቀጠና እና በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት መጠጥ ቤቶች ላይ በደረሱ የእሩምታ ተኩስ ጥቃቶች 19 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ ።

በጆሃንስበርግ ሶዌቶ መንደር ፣ በሚኒባስ ተጭነው የመጡ ጥቃት አድራሾች በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በመዝናናት ላይ በሚገኙ ሰዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ 15 ሰዎች ተገድለዋል ።

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ላይ በምትገኘው ፣ ፒተርማሪትዝበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሌላ መጠጥ ቤት ውስጥ ደግሞ ሁለት ሰዎች ካለ ልዩነት በዚህ በነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኃላ በነበረ የተኩስ ልውውጥ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 8 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ።

ፖሊስ ጥቃቶቹ ተያያዥ ስለመሆናቸው ለመናገር ጊዜው ገና መሆኑን ጠቁሞ፣ ተመሳሳይነታቸውን ግን ማጤኑን አስታውቋል-። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ እንደሌለ ተገልጿል። ሁለቱ ጥቃቶች የደረሱት ፣ ሀገሪቱ ከአፓርታይድ ዘመን ተላቃ ዴሞክራሲን መከተል ከጀመረችባቸው ሶስት አስርት ዓመታት ወዲህ ፣ በእጅጉ የከፋ ነው በተባለ የኃይል ጥቃቶችን እና አለመረጋጋት ሰደድ መመታት በቀጠለችበት ሰዓት ነው።

ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ በእጅጉ የተንሰራፋ አመጽ፣ ዘረፋ ፣ በእሳት ማጋየት እና የመሰረተ-ልማት እና ኢንደስትሪ ተቋማትን ባወደመ ጥቃት ወቅት 350 ሰዎች ሞታዋል።በኮቪድ 19 ዳፋ በተፈተነችው ሀገር በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ። ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው።

XS
SM
MD
LG