በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ጋር በዩክሬን ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን ገለጹ


የዩክሬን ህጻናት
የዩክሬን ህጻናት

ከአምስት ሰዓታት በላይ የፈጀው የዩናይትድስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ውይይት ላይ፤ ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ያላትን ህብረት እንዲሁም ደግሞ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርሰውን የሃይል ጫናን በተመለከተ ተነጋግረናል ሲሉ ከውይይቱ በኋላ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ብሊንከን ተናገረዋል።

የሁለቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ የቡድን ሃያ ስብሰባን ተክትሎ በባሊ ኢንዶኔዢያ ባደረጉት ውይይት ነው ይህንን ሊወያዩ የቻሉት። አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት ቻይና በዚህ ጦርነት ላይ ገለልተኛ በሆነ መልኩ እየተንቀሳቀሰች እንዳልሆነ እና በተ.መ.ድ ስብሰባዎች ላይም ሩሲያን በመደገፍ “ሩሲያ የምታካሂደውን ፕሮፖጋንዳ እያጎላች ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ብሊንከን የቻይናው ፕሬዘዳንት ዢ ጂንግ ፒን ከሳምንታት በፊት ለፑቲን በመደወል ከሩሲያ ጋር ለመተባበር እና በጋራ ለመቆም መወሰናቸውን በግልጽ ተናግረዋል ብለዋል። ይህን ተከትሎም የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ቻይና፤ ሩሲያ ዩክሬንን ለመጣል በምታደረገው “ልዩ የወታደራዊ ተልዕኮ” ላይ የመሳሪያ ድጋፍ ካደረገች በቻይና ምርቶች ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

XS
SM
MD
LG