ዋስትናው የታገደው፣ በተመስገን ላይ ሦስት የወንጀል ክሶችን የመሰረተው ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ መሆኑን ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ለ51 ቀናት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ፍ/ቤት ሲካታተሉ የነበሩ ስምንት “አሻራ”ና “ንስር” የተባሉ የዩቲዩብ ሚድያ ሰራተኞች በዋስ እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ቢወስንም እስካሁን አለመፈታታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡