No media source currently available
"ፊደል ኢ-ቡክ"፣ ህጻናትን ፊደል የሚያስቆጥር ፣ተረት የሚያወራ እና መዝሙር የሚዘምር የኤሌክትሪክ መጽሃፍ ነው ። የ5 ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የፈጠራ ስራ የሆነው የአማርኛ ንባብ መሳሪያ ፣ በተለይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልጆቻቸውን በቀላሉ ንባብ ለማስተማር ያላቸውን ፍላጎት ለማገዝ የተሰራ እንደሆነ ተነግሯል። ከመስራቾቹ መካከል አንዱ ከሆነው ጥላሁን ዓለማየሁ ጋር የተደረገውን ቃለ- ምልልስ ይከታተሉ።