በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ ውስጥ ለተቃውሞ በወጡ ነዋሪዎችና በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናገሩ።
ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም ሐሙስ ሰኔ/ 23/2014 ዓ.ም የተካሄደውን ሰልፍ አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች መታሰርን ተከትሎ ግጭት መቀስቀሱን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንድ ልጅ የሞተባቸው አባት፤ ልጃችውው ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ተናግረዋል።
ጉዳዩ በቀጥታ ይመለከታቸዋል ከተባለው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ቢሮ መረጃዎችን ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።