በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አንድ ትልቅ የኪነጥበበ ፈጣሪ እንዳጣን ነው የማስበው”ደራሲ እና ሀያሲ ዳንኤል ወርቁ


“አንድ ትልቅ የኪነጥበበ ፈጣሪ እንዳጣን ነው የማስበው”ደራሲ እና ሀያሲ ዳንኤል ወርቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

ቁጥራቸው በበዛ የራዲዮ እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ደራሲነቱ እና አዘጋጅነቱ የሚታወቀው ሰለሞን ዓለሙ በተወለደ በ62 ዓመቱ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ተለይቷል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጥበብ ሥራዎችን ለአድማጭ እና ለተመልካች ያቀረበው አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው ነገ ረቡዕ ሰኔ 22 /2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ከሰዓት በኃላ አድናቂዎቹ በሚገኙበት የክብር ሽኝት እንደሚደረግለት፤ የቀብር ሥነ ስርዓቱም ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ታውቋል። ከቅርብ ጓደኞቹ አንዱ የሆነው ደራሲ፣ተርጓሚን ሐያሲ ዳንኤል ወርቁ “አንድ ትልቅ የኪነጥበበ ፈጣሪ እንዳጣን ነው የማስበው” ብሎናል። /ሀብታሙ ስዩም የዕውቁን ከያኒ የቅርብ ጓደኞች እና የስራ አጋሮች ጠይቆ ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG