በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ 260 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


ከጎግል ካርታ ላይ ስክሪን ቅጂ የተወሰደ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ አካባቢን የሚያሳይ
ከጎግል ካርታ ላይ ስክሪን ቅጂ የተወሰደ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ አካባቢን የሚያሳይ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቁጥራቸው የበዛ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ አመለጥን ያሉ የይን እማኞች እና የሟቾቹ ቤተሰቦች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ጥቃቱ የደረሰባቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ መሆኑን ገልፀው በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር የተለያየ መሆኑን ይናገራሉ። ማምሻውን በዚህ ጉዳይ ላይ ዘገባ ያወጣው ሮይተር የዜና ወኪል ነዋሪዎቹ ጠቅሶ የሟቾች ቁጥር 260 መሆኑን አስነብቧል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ሸኔ መሆኑን የገለፁት የጊምቢ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሻፌ ዓለሙ ሕጻናትን እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ድርጊቱን ያወገዙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ "ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላምና ደህንነት መመለስ አሁንም ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን ነው ብለዋል።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትም በጥቃቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሠማውን ሐዘን ገልጿል ።

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት ሸኔ በማለት በአሸባሪነት የፈረጀው ሸማቂ ቡድን ግድያውን አልፈጸምኩም ብሏል።

የድርጅቱ ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኦዳ ተርቢ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የመንግሥት ኃይሎች ናቸው" ሲሉ አስተባብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ 260 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:40 0:00

/ሙሉ ዘገባውን ከተያይዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG