በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

" የእኛ የነበረውን ሁሉ እንመልሳለን" -ዘለንስኪ


በጁን 19/ 2022 የተነሳው ይሄ ምስል በዩክሬን ቸርኒዬቭ በወደመ ህንጻ አቅራቢያ የሚልፍ ወታደር ያሳያል
በጁን 19/ 2022 የተነሳው ይሄ ምስል በዩክሬን ቸርኒዬቭ በወደመ ህንጻ አቅራቢያ የሚልፍ ወታደር ያሳያል

በሩሲያ ኃይሎች ወደ ወደሙት ማይኮላይቭ እና ኦዴሳ ከተሞች ዛሬ ማለዳ ያመሩት የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ ፣ “የእኛ የነበረውን ሁሉ እንመልሳለን!” ብለዋል። ዘለንስኪ በደቡባዊው የዩክሬን ቀጠና የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል። የብዙዎችን ቤት እንዳወደመ፣ የሲቪል ተቀዋማትን አገልግሎት እና ማህበራዊ ክዋኔዎችን እንዳወከ አክለዋል። ሁሉም ወደ ነበረበት እንደሚመለስ ያለቸውን ዕምነትም አጋርተዋል ።ሩሲያ፣ ህዝባችን ካለው የመኖር ምኞት በላይ የበረከቱ ሚሳኤሎች የሏትም “ ብለዋል -ዘለንስኪ።

ይህ በእንዲህ እያለ፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር (ኔቶ) ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶትልንበርግ በዩክሬን ያለው ጦርነት የተራዘመ እና ብዙ ወጪ የሚያስወጣ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። "ቢልድ አም ሶንተግ" ለተሰኘ የጀርመን ጋዜጣ ቃላቸውን የሰጡት ስቶልትንበርግ ፣ ጦርነቱ ዓመታትን ሊፈጅ ስለሚችል መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ፣ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍም ሊቀዛቀዝ እንደማይገባ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ረጅም ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀው ፣ ዩክሬን የጦር መሳሪያ ፣ የጦር ልምምድ ድጋፍ “ከወራሪው ሀገር” በበለጠ ማግኘት እንዳለባት አስታውቀዋል።

(በዚህ ዘገባ ከአሶሼትድ ፕረስ እና ሮይተርስ የተገኙ መረጃዎች ተካተዋል)

XS
SM
MD
LG