በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግስት በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ የጣለውን ገደብ ተከትሎ በሴኔጋል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ


ከአስለቃሽ ጭስ የሚሸሹ ወጣቶች ፣ ሴኔጋል ሰኔ 17 /2022
ከአስለቃሽ ጭስ የሚሸሹ ወጣቶች ፣ ሴኔጋል ሰኔ 17 /2022

የሴኔጋል መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎችን ከታቀደው የህግ አወጭዎች ምርጫ ለማገድ መወሰኑን ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ውጥረት ጫፍ ላይ መድረሱ ተነገረ። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለተቃዋሚ ፖለቲከኛው ኦስማን ሶንኮ ድጋፋቸውን ለመስጠት ፣ ፕሬዚደንት ማኪ ሳል ተቀናቃኛቸው በምርጫው እንዲሳተፍ እንዲፈቅዱ ለመጠየቅ ወደ ጎዳና ወጥተዋል ።

አርብ ዕለት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የመኪና ጎማዎች እና የፕላስቲክ ቋቶችን በእሳት ማያያዛቸውን ተከትሎ የዋና ከተማዋ ዳካር ደቡባዊ መንደሮች በጭስ ታጥነው ውለዋል ። ሰልፈኞቹ ላይ የወረደው የአስለቃሽ ጭስ እንዲበታተኑ አድርጓቸዋል ። ቆየት ብለው ድጋሚ ወደ ጎዳናው የተመለሱት ተቃዋሚ ሰልፈኞች “ ማኪ ሳል አንባገነን ነው!” እያሉ ሲጮሁ ተሰምዋል፣ በፖሊሶች ላይም ድንጋይ ወርውረዋል ።

ከተቃዋሚዎች መካከል አንዱ የሆነው ተመራቂ ተማሪ፣ ማይሚና አይዳራ ለአሜሪካ ድምጽ ሲያስረዳ፣ “ ማኪ ሳሊ በሴኔጋል እየፈጸመ ያለው ኢ-ፍትሃዊነት ነው። እየሰራ ያለው ትክክል አይደለም” ብሏል ። ተማሪው ፣ የሴኔጋል ህዝብ በስቃይ ውስጥ እንዳለ ገልጾ ፣ ሳል ከስልጣን እንዲለቁ እንደሚሻ ተናግሯል። ከስልጣን እስኪወርዱም ድረስ ተቃውሞው በየቀኑ እንደሚቀጥልም ተናግሯል።

በሀገሪቱ ውስጥ ቁጣ ያየለው፣ የሴኔጋል የህገ-መንግስት ምክር ቤት በሀምሌ 31/2022 (የጎረጎሳዊያኑ ቀን) ምርጫ ለመሳተፍ የተሰጠውን የተቃዋሚ ዕጩዎች ዝርዝር አለመቀበሉን ተከትሎ ነው። ይሄ ውሳኔ በበኩሉ የተቃዋሚ አመራሩ ሶንኮን እና ሌሎች ተቀናቃኞች በምርጫው እንዳይሳተፉ ያግዳቸዋል ።

የምርጫው ውጤት በአሁኑ ጊዜ በፕሬዚደንቱ ፓርቲ የበላይነት የተያዘውን 165 አባላት ያሉትን የሀገሪቱን ብሄራዊ ጉባኤ ስብጥር ይወስናል።አርብ ዕለት የሀገሪቱ ፖሊስ የተቃዋሚ ፖለቲከኛውን ሶንኮን ቤት በማክበብ ከአርብ የጋራ ጸሎት ስነ-ስርዓት እና ሰልፍ ከልክሏቸዋል ።

XS
SM
MD
LG