በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአስመራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ በኤርትራ ሚዲያ ሁኔታ አስተያየት ሰጡ


ኤሪሳት ያዘጋጀው ሲምፖዚየም
ኤሪሳት ያዘጋጀው ሲምፖዚየም

የኤርትራ የመጀመሪያው ገለልተኛ የሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቢያ የሆነው ኤሪሳት በሚዲያ እና የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ የአንድ ቀን ሲምፖዚየም በዋሽንግተን ዲሲ አካሂዷል።

ቅዳሜ እለት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአስመራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ የሌላቸው ስቲቨን ዋልከር በዙም አማካኝነት ባደረጉት ንግግር በኤርትራ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት የሚዲያ ሁኔታ በሀገሪቱ ላይ ያደረሰውን አሉታዊ ተፅእኖ እና የኤርትራ ዜጎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዳይወስኑ እንዴት እንደሚያደርጋቸው ገልፀዋል።

ብዙዎች ከተለመደው የኤርትራ መንግስት ከሚደርሰው ጠንካራ ትችት ወጣ ያለ ነው ሲሉ በገለፁት ንግግር ዋልከር ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቢሮዋቸውም ሆነ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የኤርትራን ሊዓላዊነት እንደሚያከብር እና መፍትሄው ለኤርትራውያን የተተወ መሆኑንም ገልፀዋል።

ሆኖም ጉዳይ ፈፃሚው አሜሪካ በኤርትራ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አባላት አያያዝ ዙሪያ ድምጿን ስታሰማ መቆየቷን ገልፀው በተለይ በኤርትራ የመንግስት ባለስልጣናት የሚወጡ እና ሀሰተኛ ተብለው የሚታሰቡ መረጃዎችን የሚያርሙ ፅሁፎችን ብሮዋቸው በማውጣት መረጃ ላይ የተመሰረቱ ውይይቶችን ለማድረግ ሙከራዎች መድረጋቸውን ተናግረዋል።

በአንድ ቀን ጉባኤው ላይ በኤርትራ ዙሪያ በስፋት በመዘገብ የሚታወቀው ዳን ኮኔል እና ለስድስት አመታት በኤርትራ ለብቻዋ በእስር ላይ የቆየችውና አሁን በስደት ላይ የምትገኘው ይርጋለም ፍሰሃም ተገኝተዋል።

XS
SM
MD
LG