በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘ላ ኒኛ’ የአየር ንብረት ሥጋቱን እያበረታው ነው


ፎቶ ፋይል - ከኢትዮጵያ ጎዴ ከተማ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሃርጉዶ የተባለ ቦታ በድርቅ ምክኒያት የሞቱ በጎችን ሰዎች ተሰብስበው እየተመለከቱ።
ፎቶ ፋይል - ከኢትዮጵያ ጎዴ ከተማ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሃርጉዶ የተባለ ቦታ በድርቅ ምክኒያት የሞቱ በጎችን ሰዎች ተሰብስበው እየተመለከቱ።

“ላ ኒኛ” እየተባለ የሚጠራው የአየር ንብረት እስከመጪው ዓመት እንደሚቀጥልና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚታየውን አሳሳቢ ድርቅም ሊያባብስና ሊያራዝመው እንደሚችል የአየር ትንበያ ባለሞያዎች ገለጹ።

“ላ ኒኛ” የተባለው የአየር ሁኔታ ክስተት በማዕከላዊና በምስራቅ ሰላማዊ ውቅያኖስ የባህር ወለል በከፍተኛ ደረጃ መቀዝቀዝን ይመለከታል።

የቪኦኤዋ ሊሳ ሽላይን የዓለም የአየር ትንበያ ድርጅት ቃል አቀባይን ክሌር ኑሊስ ጠቅሳ እንደዘገበችው

“ላ ኒኛ” የአየር ሙቀትንና ዝናብን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲያዛባ ድርቅንና በጎርፍ መጥለቅለቅንም ያባብሳል።

በአፍሪካ ቀንድና በደቡብ አሜሪካ እየታየ ያለው ድርቅ፥ በደቡብ ምስራቅ እሲያና አውስትራሊያ የታየው ከተለመደው መጠን በላይ ዝናብ፥ እንዲሁም በአትላንቲክ የሚታየው ጠንካራ አውሎ ነፋስ የ”ላ ኒኛ” ውጤቶች መሆናቸውን ክሌር ጨምረው ተናግረዋል።

በተፈጥሮ የሚታዩ እንደ “ላ ኒኛ” ያሉ የአየር ለውጦች አሁን እየተከሰቱ ያሉት የሰው ልጅም ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ነው። የዓለም የአየር ትንበያ ድርጅት፤“ላ ኒኛ” አየርን የማቀዝቀዝ ተጽኖ ቢኖረውም አጠቃላይ የዓለም ሙቀት ግን እያሻቀበ እንደሚገኝ ገልጿል።

ይህም ቀድሞውንም አራት የዝናብ ወቅቶች ያለፉባትና ሚሊዮኖች በረሃብ በሚሰቃዩባት አፍሪካ ቀንድ አስቸጋሪና አደገኛ ሁኔታ ይዞ ይመጣል። ቃል አቀባይዋ ኑሊስ በሶማሊያ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ወራት ይጠበቅ የነበረው ዝናብ አለመምጣቱን አስታውሰዋል።

አሁን ደግሞ በመጪው ኅዳርና ታኅሣሥ የሚጠበቀው ዝናብ ላይመጣ እንደሚችል ሲገመት፥ ይህ የሚሆን ከሆነ ደግሞ የሰብአዊ ቀውሱ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ስጋታቸውን አጋርተዋል።

ባለፈው ወር 14 የሚሆኑ የአየር ንብረትና የሰብአዊ ድርጅቶች ባወጡት የጋራ ማስጠንቀቂያ በሶማሊያ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ የሚታየው አደገኛ የድርቅ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ጅምላ ረሃብ ሊያመራ ይችላል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG