በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ የሩሲያ ከበባ አለም አቀፍ የምግብ እጥረት ሊያስከትል ይችላል አሉ


In this image from video provided by the Ukrainian Presidential Press Office, Ukrainian President Volodymyr Zelenskyy speaks from Kyiv, Ukraine, early Sunday, March 20, 2022. (Ukrainian Presidential Press Office via AP)
In this image from video provided by the Ukrainian Presidential Press Office, Ukrainian President Volodymyr Zelenskyy speaks from Kyiv, Ukraine, early Sunday, March 20, 2022. (Ukrainian Presidential Press Office via AP)

አርባ ሁለት ሃገራት በሚሳተፉበት በሲንጋፖር ሻንጋሪላ እየተካሄደ ባለው ከፍተኛ የመሪዎች የጸጥታ ስብሰባ ላይ ዛሬ በቪዲዮ የተሳተፉት ዘለንስኪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያካሄደችው ወረራ ለብዙ ሃገራት የምጣኔ ሃብት ውድቀት እንደሚያስከትል እና የአለም አቀፍ የአቅም ተዋረድን እንደሚጎዳ አስጠንቅቀዋል። ሰለዚህም ጠንካራ የሆነ እርምጃ ይደረግ ሲሉ አስምረውበታል።

ዘለንስኪ “ስለድጋፋቹ አመስጋኝ ነኝ። ነገር ግን የምታደርጉት ድጋፍ ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለራሳችሁም ጭምር ነው” ብለዋል። አያይዘውም “በዩክሬን የጦርነት አውድማዎች ላይ ድንበሮች እና የዚህች አለም የወደፊቱ እጣፈንታ እየተወሰነ ነው” ሲሉ አክለዋል።

ዘለንስኪ የሩሲያ ወታደሮች የአለም ከፍተኛ የእህል አቅራቢ ከሆነች ዩክሬን እህል እንዳይወጣ በመገደባቸው እጅግ ብዙ አፍሪካ እና የእስያ ሃገራት እርሃብ እና የምግብ እጥረት እንዲጋረጥባቸው አድርገዋል።” ብለዋል።

የሩሲያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የሃይል አቅርቦትን በመገደብ ዋጋ እንዲወደድ ያደረገ ሲሆን ይሄው ስልት አቅርቦትም ላይ በተመሳሳይ እየተተገበረ ነው። ዘለንስኪ ሩሲያ የጥቁር ባህር እና የአዞቮ ባህርን በመዝጋት የዩክሬን እህል ወደ አለም ገበያ እንዳይደርስ ከልክላለች። ይሄም ዩክሬንን ብቻ ሳይሆን መላው አለምን ይጎዳል ብለዋል።

ሩሲያ አደገኛ ብሔርተኞች ስትል የገለጸቻቸውን የዩክሬን ወታደራዊ ሃይል ለማዳከም ስትል “ልዩ ተልዕኮ” ስትል የጠራችውን እያካሄደች መሆኑን አስታውቃለች።

ዘለንስኪ “ጦርነቱ ዩክሬን ላይ እየተካሄደ መሆኑን እና ወደ ሩሲያ ምድር ዘልቀን የመግባት ፍላጎት እንደሌለን እና ዩክሬናዊያን እየሞቱ መሆኑን አስታውሱ” ሲሉ መሪዎቹን አሳስበዋል።

በሲንጋፖር የዩክሬን አምባሳደር ካተሪያና ዘለኔኮ ሃገሪቷ በአስቸኳይ ከፍተኛ ድጋፍ ትሻለች ያሉ ሲሆን “ጊዜ የሚወስድ መሆኑን እንረዳለን ነገር ግን የሌለን ነገር ጊዜ ነው” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG