በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተራዘመው የላኒንኛ የአየር ለውጥ የምስራቅ አፍሪካ ድርቅ በአስከፊ ሁኔታ እንዲባባስ ያደርጋል ተባለ


Ethiopia Drought EU
Ethiopia Drought EU

እ.ኤ.አ በ2020 ዓ.ም የጀመረው ላኒንኛ የተሰኘው የአየር ንብረት ሁኔታ እስከመጪው ነሃሴ እና እስከቀጣይ ዓመት ሊዘልቅ እንደሚችል የአለም የሜትሮሎጂ ተቋም አስታወቀ። ይሄ ሁኔታም በአፍሪካ ቀንድ የተራዘመ እና አስከፊ የሆነ ድርቅ እንዲኖር እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ላኒንኛ በሰሜናዊ የምድር ወገብ አካባቢ ባለው የፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የሚከሰት የአየር መቀዝቀዝ ሲሆን የተቋሙ ቃል አቀባይ ክሌር ኑሊስ ላኒንኛ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የጎርፍ አደጋ ያባብሰዋል ይላሉ። “በአሁን ሰዓት በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያለው ድርቅ የላኒንኛ መገለጫ ሲሆን በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አውስትራሊያ ከተገቢው በላይ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ ያለው ለዚሁ ነው” ብለዋል።

በአሁን ሰዓት ላኒንኛን ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ የአየር ንብረት ለውጦች በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የሚመጡ መሆናቸውን የአለም የሜትሮሎጂ ተቋም አስታውቋል። ምንም እንኳን ላኒንኛ ቀዝቃዛ አየር ቢሆንም የአለም ሙቀት መጠን ጨምሯል። ይህም በምስራቅ አፍሪካ ለአራት ተከታታይ አመታት በቂ የሆነ ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ብዙዎች በበረታ እርሃብ እንዲሰቃዩ አድርጓቸዋል።

ባለፈው ወር ላይም 14 የሜትሮሎጂ እና የሰብዓዊ ጉዳይ ተቋማት በጋራ ማስጠንቀቂያ ያወጡ ሲሆን በሶማሊያ፣ ኬኒያ እና ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅ ከባድ የርሃብ አደጋ ደቅኗል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG