በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካፒቶል የጃንዋሪ 6 ኮሚቴ ሪፖርት ለህዝብ መቅረብ ጀመረ


ኮሜቴውን በሊቀመንበርነት የሚመሩት የሚሲሲፒው ዴሞክራት ቤኒ ቶምሰን ምክትል ሰብሳቢዋ ሊዝ ቼኒ የመክፈቻ ንግግር ሲያደረጉ
ኮሜቴውን በሊቀመንበርነት የሚመሩት የሚሲሲፒው ዴሞክራት ቤኒ ቶምሰን ምክትል ሰብሳቢዋ ሊዝ ቼኒ የመክፈቻ ንግግር ሲያደረጉ

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የጃንዋሪ 6 አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን ለህዝብ ማቅረብ ጀመረ።

ኮሚቴው ይህንን ሪፖርቱን በዋሺንግተን ዲሲ ሰዓት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ለህዝብ በቀጥታ የሚተላለፈውን ሪፖርቱን ማቅረብ የጀመረው ወደ ማጣራት ሥራው ከገባ ወደ አንድ ዓመት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ነው።

ኮሚቴው ግኝቶቹን፣ ማስረጃዎችንና እማኞችን የሚያሰማው በመጭዎቹ ወራት መደዳውን እንደሚሆን ተነግሯል።

ኮሚቴው ለህዝብ የሚያቀርበው ሪፖርት በቴሌቪዥን፣ በራዲዮና በሌሎችም መገናኛ ብዙኃን በቀጥታ የሚተላለፍ ነው።

በቀደሙት ወራትም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ደጋፊዎች ናቸው በሚባሉ ሰዎች ላይ ምርመራ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ምርመራው አሁንም በኮሚቴውና በሃገሪቱ ህግ አስከባሪ ተቋማት እንደቀጠለ መሆኑን የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ሪፐብሊካኗ የዋዮሚንግ እንደራሴ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል።

ከዘጠኙ የተወካዮች ምክር ቤቱ ኮሚቴ አባላት ሰባቱ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ሲሆኑ ሁለቱ ሪፐብሊካን ናቸው።

ኮሜቴውን በሊቀመንበርነት የሚመሩት የሚሲሲፒው ዴሞክራት ቤኒ ቶምሰን ናቸው ሪፖርት የማቀረቢያውን መድረክ የከፈቱት።

ሊዝ ቼኒ ሲቢኤስ ኒውስ ለሚባለው የዜና አውታር ባለፈው ዕሁድ ሰጥተውት በነበር ቃለ ምልልስ ሰዉ ለሚያቀርቡት ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በዚያ ቃለ ምልልስ “የዲሞክራሲ ሥርዓት ካልተንከባከብንና ካልጠበቅነው ሊፈረካከስ የሚችል መሆኑን ሰዉ ሊገነዘብ ይገባል” ብለዋል።

ያለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ማረጋገጫ ድምፅ በህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ውስጥ ከሚቀርብበር ጊዜ ጥቂት ቀደም ብሎ የያኔው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በምክር ቤት አቅራቢያ ከተካሄደውና ተገኝተውበት በነበረ ሰልፍ ላይ እርሳቸው መሸነፋቸው የተነገረበት ውጤት “የተሰረቀ” መሆኑን ተናግረው “እንደገሃነም ተፋለሙ” የሚል ጥሪ አሰምተው እንደነበር ተዘግቧል።

ሪፐብሊካኑ እንደራሴዎችና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ይህንን የኮሚቴውን ሥራ “የፖለቲካ ላም ባልዋለበት ...” ነው እያሉ እያጣጣሉት ነው።

የዚህን የኮሚቴውን ሥራ የሚመለከቱ ዘገባዎችን በተከታታይ እናቀርባለን።

የመክፈቻውን ሙሉ ሥነ ሥርዓት ከታች የተያያዘውን ማገናኛ ተከትለው ይመልከቱ።

WATCH: Public Hearings to Detail 2021 Riot at US Capitol (voanews.com)

XS
SM
MD
LG