በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 “መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ሕይወት መለወጥ እንፈልጋለን”  - የተኪ የወረቀት ቦርሳዎች ማምረቻ መስራች


 “መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ሕይወት መለወጥ እንፈልጋለን” - የተኪ የወረቀት ቦርሳዎች ማምረቻ መስራች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:43 0:00

“መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ሕይወት መለወጥ እንፈልጋለን” - የተኪ የወረቀት ቦርሳዎች ማምረቻ መስራች

በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ/ መስማት የተሳናቸው ሴቶች ለመሰረቱት የወረቀት ቦርሳዎች አምራች 550 ሺህ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

መስማት የተሳናቸው ዜጎች ሥራ የማግኘት እድላቸው የተመናመነ መሆኑን የምትገልጸው የድርጅቱ መስራች እና ምክትል ስራ አስኪያጅ ሚሚ ለገሰ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ከዚህ አንጻር ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናግራለች፡፡

“ተኪ” ለተባለው የወረቀት ቦርሳዎች አምራች የተደረገውን ድጋፍ ይፋ ያደረጉት በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጄከብሰን ሲሆኑ በዕለቱም “ይህ ድጋፍ የተደረገው፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው ድርጅቱ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረውን ሥራ ማበረታታት፣ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት 200 ለሚሆኑ መስማት የተሳናቸው ሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ነው” ብለዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ/ የተደረገው ድጋፍ፣ በመደበኛ ውድድር የሥራ ዕድል ለማግኘት የሚፈተኑ መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ከመጥቀም ባለፈ፣ ሥራቸውን ለማጠናከር እንደሚረዳቸው የተኪ የወረቀት ቦርሳዎች ማምረቻ ድርጅት ሠራተኞች እና ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ

XS
SM
MD
LG