የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ትላንት የነዳጅ ቁፋሮ በሚካሄድባቸው ሶስት አካባቢዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የፕሮጄክቱ አስተዳደርና ክትትል ክፍተት እንደነበረበት የሶማሌ ክልል ገልጿል። ነዳጅ የማውጣቱ እና ለጥቅም ዝግጁ የማድረጉ ስራ የህዳሴው ግድብን ሁለት እጥፍ በጀት የሚፈልግ በመሆኑ ፕሮጄክቱ ረዘም ያለ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችልም ተገልጿል።
በሱማሌ ክልል የነዳጅ ቁፋሮ ፕሮጄክቱ አካል ነው የተባለ እና እስካሁን ሳይከፈል የቆየ 113 ሚሊዮን ብር ለአካባቢው ማህበረሰብ ልማት እንዲውል የማዕድን ሚኒስቴር ለሶማሌ ክልል አስረክቧል።
በተጨማሪም የነዳጅ ቁፋሮ ይካሄድባቸው በነበሩ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ ከዚህ በፊት በአለም አቀፍ የመገናና ብዙሃን ሲዘገብ የነበረው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ነው ሲል ክልሉ አስተባብሏል።