በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል አልማ የተነሳችው ኢትዮጵያዊት - ርብቃ ሀይሌ


የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል አልማ የተነሳችው ኢትዮጵያዊት - ርብቃ ሀይሌ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00

የፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ልጅ፣ ርብቃ ሀይሌ የስደት ህይወትን ለማሸነፍ የረዳትን ጥራት ያለው ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ የኢትዮጵያ ትምህርት ተነሳሽነት ተቋም በመመስረት ዓለም አቀፍ ድረጃውን የጠበቀ ትምህርት መስጠት ጀምራለች። ተቋሙ በደብረብርሃን የከፈተው ሀይሌ ማናስ አካዳሚ አዳሪ ትምህርትቤት 400 የሁለተኛ ድረጃ ተማሪዎችን ከመላው ኢትዮጵያ ተቀብሎ ማስተማር የሚችል ሲሆን የአመራርና ማህበረሰብን የመገንባት ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን የማፍራት እቅድ አለው።

የጥንታዊ ኢትዮጵያን ታሪክ ያጠኑት ሊቅ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ልጅ፣ ርብቃ ሀይሌ በስደት ለ25 አመታት በኖረችበት አሜሪካን ሀገር የስደት ህይወትን ለማሸነፍ እና በህግ ትምህርት ትልቅ ቦታ ለመድረስ የረዳትን ጥራት ያለው ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ የኢትዮጵያ ትምህርት ተነሳሽነት ተቋም በመመስረት ዓለም አቀፍ ድረጃው የጠበቀ ትምህርት መስጠት ጀምራለች። ተቋሙ በደብረብርሃን የከፈተው ሀይሌ ማናስ አካዳሚ አዳሪ ትምህርትቤት 400 የሁለተኛ ድረጃ ተማሪዎችን ከመላው ኢትዮጵያ ተቀብሎ ማስተማር የሚችል አቅም ያለው ሲሆን የአመራርና ማህበረሰብን የመገንባት ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን የማፍራት እቅድ አለው። ስመኝሽ የቆየ ርብቃ በተለይ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እያደረገች ስላለችው ጥረት አነጋግራታለች።

XS
SM
MD
LG