በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስደተኛ ልጆች ለምን ከአሜሪካ ተወላጅ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ይኖራቸዋል?


ስደተኛ ልጆች ለምን ከአሜሪካ ተወላጅ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ይኖራቸዋል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት ስታንፎርድ እና ፕሪንስተን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን በጋራ ያካሄዱት ጥናት ነባር ተወላጅ ከሆኑ አሜሪካውያን ይልቅ በስደት ከየትኛውም ዓለም የሚመጡ ተማሪዎች በትምህርታቻው ለተሻለ ለስኬት እንደሚበቁ ያሳያል። ወላጆቻቸው በስደት የመጡ ተማሪዎችም እናትና አባቶቻቸው ከሀገራቸው ይዘውት በሚመጡት የትምህርት ድረጃ እና ልምድ ምክንያት በትምህርታቸው የተሻለ ድጋፍ እንደሚያገኙም አመልክተዋል።

ሮቤል ልዑል ሰገድ ላለፉት ስድስት አመታት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከተከታተለበት የፎርክ ዩኒየን ወታደራዊ አካዳሚባለፈው ሳምንት ሲመረቅ በትምህርቱ የ4.602 ከፍተኛ ውጤት ከማስመዝገብ በተጨማሪ፣ የተመራቂ ተማሪዎቹንወክሎ ንግግር አድራጊም ነበር።

"በመጀመሪያ ዛሬ እዚህ እንድቆም የረዳችን እናቴን እግዚአብሄር ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ። እንዲሁም በፉማ በነበረኝየስድስት አመት ቆይታ ይዣቸው የተጓዝኳቸውን እና በህይወቴ የምኮራባቸውን እሴቶች እንድቀርፅ የረዱኝን ቤተሰቦቼንእና ጓደኞቼን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ።"

ሮቤል በትምህርት ቤት ቆይታው በጎበዝ ተማሪነቱ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ቤቱ ውስጥ በነበረው የአመራር ብቃት እናከትምህርቱ ጎን ለጎን በሚያደርጋቸው ተሳትፎዎች ነው መሆኑን መምህራኖቹም ይመሰክራሉ።

"እዚህ ትምህርት ቤት ማስተማር ከጀመርኩ ከሶስት አመት በኃላ ነው ሮቤል እዚህ ትምህርት ቤት የገባው። የሚወደድየ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበር። አርት እና ቲያትር አስተምሬዋለሁ። በኔ ክፍል በመማሩ ደስተኛ ነበርኩ። ከትንሽ ልጅነትወደሚከበር፣ የሚወደድ እና ሀላፊነ የሚሰማው ወጣትነት ሲያድግ ማየቴ ከምኮራባቸው ነገሮች አንዱ ነው።"

በአሜሪካን አገር የሚገኙት ስታንፎርድ እና ፕሪንስተን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ያጠኑት ጥናት ልክ እንደሮቤልከየትኛውም የአለም ክፍል በስደት ወደ አሜሪካን አገር ከመጡ ወላጆች የተወለዱ ወይም በቀጥታ በስደት የመጡተማሪዎች ከአሜሪካዊ ወላጆች ከሚወለዱ የተሻለ በትምህርታቸው ለስኬት እንደሚበቁ ያሳያል። እንደምክንያትምስደተኞች ከሀገራቸው ይዘውት የሚመጡት አላማ፣ ፅናት እና የትምህርት ደረጃ እንደምክንያት እንደሚጠቀስያስቀምጣል።

የሮቤል እናት ወይዘሮ የትናየት እሳቱ እ.አ.አ በ1987 በስደት ወደ አሜሪካን ሀገር ከመጣች በኃላ በትምህርቷና በሙያየተሳካላት የቤት ሽያጭና ግዢ ባለሙያ እንዲሁም ቤተሰቦች እንዴት ሀብትን መገንባት እንደሚችሉም አማካሪ ናት ።ከሮቤል በተጨማሪ ታላቅ ወንድሙንም ለተመሳሳይ ስኬት ማብቃት እንዴት እንደቻለች ታዲያ እንዲህ ታስረዳለች።

ይህ ጥረቷ ተሳክቶ ዛሬ ልጆቿ የደርሱበትን ስኬት ስትገልፀው ታዲያ ' እጅግ በጣም አርኪ ነው' ትላለች።

ወይዘሮ የትናየት ታዲያ ለራሷም ስኬት ሆነ ልጆቿ ዛሬ ለደረሱበት የትምህርት ደረጃ መሰረት የሆናት በኢትዮጵያ ስታድግበቤተሰቦቿ ውስጥ ለትምህርት ሲሰጥ ያየችው ዋጋ እና ወደ አሜሪካን ሀገር ከመጣች በኃላ በኖረችበት ህብረተሰብ ትልቅቦታ ለመድረስ ትምህርት ያለውን ቦታ በመረዳቷ እንደሆነ ትገልፃለች።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሁለቱ የአሜሪካ ፓርቲዎች ከሚከራከሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። ስደተኞች ወደአሜሪካ ሲመጡ ሸክም እንደሚሆኑ፣ ለወንጀል መጨመር ምክንያት እንደሆኑ እና የመሳሰሉ ክሶች ይቀርቡባቸዋል።የስታንፎርድ እና ፕሪንስተን ትምህርት ቤቶች ጥናት ግን የሚያሳየው እውነታው ተቃራኒው መሆኑን ነው።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተምረው ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለማግኘት ወደ አሜሪካን ሀገርዩንቨርስቲ ኦፍ ኦሪገን ያቀኑት እና አሁን በሚኖሶታ የሚገኘው ሀምሊን ዩንቨርስቲ ፣ የኮሚዩኒኬሽን የትምህርት ክፍልረዳት ፕሮፌሰር ሆነው የሚያገለግሉት ዶክተር እንዳልካቸው ጫላ በተለይ ስደተኛ ተማሪዎች ለምን ስኬታማ እንደሚሆኑእንዲህ ያስረዳሉ።

የሀገሩ ተወላጅ፣ ነባር አሜሪካውያንስ በትምህርት ያላቸው ስኬት ከስደተኛ ተማሪዎች ለምን ያነሰ ይሆናል - ዶክተርእንዳልካቸው ምላሽ አላቸው።

በስታንፎርድ ዩንቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አብራሚትዝኪ እንደሚያስረዱት እነዚህ ተማሪዎች ወላጆቻቸውበአሜሪካን ዝቅተኛ ስራ ቢሰሩ እንኳን በነበሩባቸው ሀገራት የተማሩ እና በሙያቸው ይሰሩ የነበሩ መሆኑ ለልጆቻቸውስኬት ይጠቅማል ይላሉ።

ጥናቱን ያጠኑት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዳመለከቱት ስደተኞች የሀገሩ ተወላጆች ሲሰሯቸው የማይፈልጓቸውንስራዎች በመስራት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፍተት እንዴት መሙላት እንደቻሉም አመልከተዋል። በቀጣይ አሜሪካስደተኞችን በተመለከት ልትከተል የምታስበውን ፖሊሲ ከመቅረጿ በፊትም በጥናታቸው ያገኟቸውን ግኝቶች ግምትውስጥ እንደሚገባም ተስፋ ያደርጋሉ።

XS
SM
MD
LG