በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ አምራቾች የስንዴና የኃይል እጥረት ገጥሟቸዋል


የናይጄሪያ አምራቾች የስንዴና የኃይል እጥረት ገጥሟቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:42 0:00

የናይጄሪያ አምራቾች የስንዴና የኃይል እጥረት ገጥሟቸዋል

የናይጄሪያ አምራቾች በሩሲያና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የእህል ዋጋ ማሻቀብ እያማረሩ ነው። በተለይ “የስንዴ ዋጋ የማይቀመስ ሆኗል” ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጦርነቱ ባለፈው ታኅሣስ ከመጀመሩም በፊትም ቢሆን ሀገሪቱ በነዳጅና በኃይል እጥረት ሳቢያ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ተመትታለች።

ማቹኩ ኦሪዙ ከስድስት ዓመታት በፊት የነበረችበትን የህክምና ላቦራቶሪ ሥራ አቁማ ነበር የህፃናት ምግብ ማምረት የጀመረችው።

በቆሎ፣ ሩዝ እና ቡናማ ስንዴ እየተጠቀመች ተጨማሪ አልሚ ምግብ እያዘጋጀች ለአከፋፋዮች ትልካለች።

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በፈጠረው የአቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት ግን ከዚህ በኋላ ስንዴ የምታገኘው መቼ እንደሆነ አታውቅም። እሷ እንደምትለው የስንዴ እጥረት በሌሎች ሰብሎች ዋጋ ላይም ተፅእኖ እያሳደረ ነው።

“ስንዴ፣ አጃ እና የስኳር ድንች ዱቄት ቀላቅዬ እጠቀማለሁ። የማልዋሽህ ነገር እነዚህን ነገሮች ለማግኘትንኳ አዳጋች ሆኗል። የዋጋ መጨመሩ ብቻ አይደለም። ስንዴ ማግኘት እጅግ አዳጋች ሆኗል፤ እኔ ደግሞ በጅምላ ነው የምገዛው። አቅራቢዎቼጋ ብዙ ግዜ ደውያለሁ” ትላለች ኦሪዙ።

ኦሪዙ በስንዴ ምትክ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እያሰበች ቢሆንም ምናልባት ደንበቿ ‘ላይፈልጉት ይችሉ ይሆናል’ የሚለው ጉዳይ ያሳስባታል።

“አምርተህ ከሸጥክ በኋላ ትርፍ የማታገኝ ከሆነ ችግር ነው። እንዲህ የሚሆን ከሆነ ምኑን ንግድ ሆነው። አሁን ስንዴን በሌላ ሰብል ለመተካት ጥናት እያደርኩ ነው። አሁን ለግዜው ያሰብነው ‘አቻ’ የተባለውን እህል ለመጠቀም ነው። እስከ ቅዳሜ ድረስ እወስናለሁ።”

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት እንደሚለው ጦርነቱ እንደተጀመረ

የስንዴ ዋጋ በ 5.7 ከመቶ ተወድዷል። ነገር ግን ከጦርነቱ ቀድሞም ቢሆን በናይጄሪያ የስንዴ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ዋጋው 30 ከመቶ አሻቅቦ ነበር። በሃገሪቱ የሚመረተው ስንዴ የሚሸፍነው የፍላጎቱን 10 በመቶ ብቻ መሆኑን የናይጄሪያ ስንዴ አምራች ገበሬዎች ማኅበር ይናገራል።

ናይጄሪያ ባለፉት ተከታታይ ሁለት ዓመታት፤ በ2020 እና በ2021 ዓ.ም. 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ስንዴ ከአሜሪካና ከሩሲያማስገባቷል የሃገሪቱ ስታትስቲክ ቢሮ አመልክቷል።

የናይጄሪያ አምራቾች ማኅበር እንደሚለው ደግሞ ችግሩ የእህል አቅርቦት እጥረት ብቻ

አይደለም። የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩም በፊት ሀገሪቱ በነዳጅና ሃይል እጥረት፣ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ በወደቀ መሠረተ ልማትና በፀጥታ እጦት ተመትታለች።

ሴጉን አጃዪ-ካዲሪ የናይጄሪያ አምራቾች ማኅበር መሪ ናቸው።

“ሰላምና ደህንነት ያለመኖር በአቅርቦት ላይ ችግር ፈጥሯል። በዚህ ችግር ውስጥ ያሉት አካባቢዎች ደግሞ ዋና ሰብል የሚመረትባቸው አካባቢዎች ናቸው። ከደህንነቱ መጥፋት በተጨማሪ መንገዱ ፈርሷል። ባሉብን ችግሮች ላይ ተጨምሮ አሁን ጭራሽ ሰዎች ማረስ የማይችሉበት ደርጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል ካዲሪ።

የመብራት መቆራረጡ የተከሰተው የሃገሪቱ ዋና ቋት ባለፈው ጥር በተደጋጋሚ በመበላሸቱ መሆኑን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

እንደ ኦስማን መሃመድ ያሉ ዳቦ ጋጋሪዎች ኤሌክትሪክ ባለመኖሩ ናፍጣ ወደ መጠቀም ዞረዋል። “የናፍጣውም ዋጋ ቢሆን የሚቀመስ አልሆነም”ይላል ኦስማን። በዚህ ዓመት ብቻ ዋጋው በሦስት እጥፍ ጨምሯል።

“በየቀኑ ብዙ ናፍጣ እንጠቀማለን ምክንያቱም መብራት የለም። ስለዚህ ብዙ ናፍጣ መግዛት አለብን። ምርታችንም ላይ ሆነ የዳቦ ዋጋ ላይ ተጽህኖ አሳድሮብናል” ይላል መሃመድ።

የነዳጅ እጥረቱን ያስከተለው ባለፈው ጥር 170 ሚሊዮን ሊትር የተበከለ ነዳጅ ከገበያ እንዲወጣ በመደረጉ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

ለአሁኑ ግን እንደ ኦሪዙ እና መሃመድ ያሉ ነጋዴዎች መጭው ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋበማድረግ ሥራቸውን እንደነገሩ ማከናወን ቀጥለዋል።

XS
SM
MD
LG