ዶክተር ካትሪን ሀምሊን እና ባለቤታቸው ዶክተር ሪጅ ሀምሊን ከ60 አመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በቀድሞውልዕልተ ፀሀይ ሆስፒታል የአዋላጅ ነርሶች ኮሌጅ ለማቋቋም ነበር። ሆኖም በርካታ ወጣት ልጃገርድ ሴቶች በፌስቱላ በሽታተጠቅተው ሲያዩ ልባቸው በመነካቱ 'መርዳት አለብን' በሚል የፊስቱላ ቀዶ ጥገና ለብቻ ነጥለው መስራት ጀመሩ።የታካሚዎች ቁጥር ግን ሆስፒታሉ ከሚችለው አቅም በላይ በመሆኑ እ.አ.አ በ1974 የአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታልንመሰረቱ።
የሀምሊን እንክብካቤ በመባል የሚታወቀው የህክምና አሰጣጥ ልጃገረዶች እና ሴቶች ከፊስቱላ በሽታ ታክመው ሽንትንካለመቆጣጠር ችግር እንዲድኑ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ብቻ ሳይሆን ተያይዘው ከሚመጡ እንደ ጭንቀት፣ ተስፋ መቁረጥእና የመገለል ስሜት እንዲያገግሙ ማድረግንም እንደሚያካትት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ማሞገልፀውልናል።
ወደ ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል የሚመጡ ታካሚዎች ከአካላቸው እኩል የአይምሮ ጤናቸው እንዲስተካከል እና በራስመተማመናቸው እንዲመለስ ታዲያ ደስታ መንደር ተመሰረተ። ከአዲስ አበባ 17 ኪሎሜትር ወጣ ብሎ ቡራዩ ወይምበቀድምሞ አጠራሩ ታጠቅ የጦር ሜዳ አካባቢ የተመሰረተው ይህ መንደር ከጤና እንክብካቤ ባሻገር ተከታታይ የባለሙያምክር በመስጠት፣ መሰረታዊ ትምህርት እና የሙያ ስልጠናም ይሰጣል።