በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆርጅ ፍሎይድ የተገደለበት 2ኛ ዓመት በተለዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው


ፎቶ ፋይል - ጆርጅ ፍሎይድ ሁለተኛ  ዓመት ቤተሰብ የአንድ ዓመት መታሰቢያ ሲያደርጉ፣ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ሚኒያፖሊስ ውስጥ እአአ 25/2021
ፎቶ ፋይል - ጆርጅ ፍሎይድ ሁለተኛ  ዓመት ቤተሰብ የአንድ ዓመት መታሰቢያ ሲያደርጉ፣ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ሚኒያፖሊስ ውስጥ እአአ 25/2021

በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ሚኒያፖሊስ ውስጥ፣ እኤአ ግንቦት 25/2020፣ በፖሊስ የተገደለውን ጥቁሩን ጆርጅ ፍሎይድ ሁለተኛ ዓመት ለመዘከር፣ እስከ ቅዳሜ የሚዘልቀው ዝግጅት፣ ትናንት ረቡዕ በሻማ ማብራት ስነ ሥርዓት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ማህበረሰባዊ አንቂዎች ከሻማ ማብራቱ በተጨማሪ ሴንትፖል በሚገኘው በአገረ ገዥው መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ሰልፍ ማድረጋቸውን የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ዝግጅቱ ዛሬ ሐሙስም የሚቀጥል ሲሆን፣ ከፖሊስጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ የጥቁር አሜሪካውያን ቤተሰቦችና ወዳጆች መሳባሰብ እንደሚካሄድ ተዘግቧል፡፡

ነገ ዓርብም እንዲሁ፣ ጆርጅ ፍሎይድ በተገደለበት ስፍራ፣ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ በማግስቱ ቅዳሜ የሙዚቃ ትርኢት የሚቀርብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG