በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ፕሬዝዳንት 'ከሩሲያ ጋር የሚካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያበቃው በዲፕሎማሲ ነው' አሉ


ፋይል - የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዚለንስኪ ለደቡብ ኮርያ ፓርላማ አባላት በቪዲዮ ንግግር ሲያደርጉ የሚያሳይ ምስል
ፋይል - የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዚለንስኪ ለደቡብ ኮርያ ፓርላማ አባላት በቪዲዮ ንግግር ሲያደርጉ የሚያሳይ ምስል

በዲፕሎማሲያዊ ስምምነት መሆኑን ትላንት በሀገራቸው የቴሌቭዥን ጣቢያ ባደጉት ቃለ መጠይቅ ተናገሩ።

ዚለንስኪ "በጦር ውጊያ ማሸነፍ እጅግ አስቸጋሪ እና ደም አፋሳሽ ነው። ግን የሚጠናቀቀው በዲፕሎማኒ ነው። ይህእንደሚሆን ርግጠኛ ነኝ" ነው ያሉት። አክለውም "በድርድር ጠረጴዛ ላይ ካልተቀመጥን በስተቀር ልንጨርሳቸውየማንችላቸው ነገሮች አሉ" ብለዋል።

የዩክሬን መሪው ይህን የተናገሩት ሀገራቸው፣ በማሪዮፖል ከተማ አዞቭስታል የብረት ማምረቻ ለሳምታት ሲዋጉ ቆይተውለሩሲያ እጅ የሰጡ ወታደሮቻቸውን ለማስመለስ ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው። የጦር ምርኮኞቹ ደህንነትበተባበሩት መንግስታት፣ ቀይ መስቀል እና የሩሲያ ፌዴሬሽን እጅ መሆኑን የገለፁት ዚለንስኪ የዩክሬን የደህንነትአገልግሎት በድርድር ለማስመለስ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ ትላንት በምስራቅ ዩክሬን የምታደርገውን ውጊያ አጠናክራ በመቀጠል መድፍ፣ ሮኬት እናአውሮፕላኖችን በመጠቀም ዶኔትሰክ እና ሉሀንስክ ከተሞችን ደብድባለች። ዩክሬናዊ ሲቪሎች እና ወታደራዊባለስልጣናት እንዳስታወቁትም በድብደባው መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል፣ ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል። ዚለንስኪ ሁለቱአካባቢዎች በሚገኙበት ዶምባስ ቀጠና ያለው ሁኔታ "ሲኦል" መሆኑን ገልፀው "አካባቢው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል" ብለዋል።

በጦርነቱ መጀመሪያ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪየቭን መቆጣጠር ሳይችሉ የቀሩት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ አሁን ዋናትኩረታቸው ዶንባስ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG