በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ገበያ ለማቋቋም ሥምምነት ተፈረመ

በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ኤፍኤስዲ አፍሪካ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ መካከል ስምምነት ሲፈረም
በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ኤፍኤስዲ አፍሪካ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ መካከል ስምምነት ሲፈረም

“ኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ” የተባለ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ገበያ ለማቋቋም የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ። ሥምምነቱ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ኤፍኤስዲ አፍሪካ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ መካከል በተፈረመው ሥምምነት መሰረት ይቋቋማል የተባለው የኢትዮጵያ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ገበያ “ኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ኢሲኤክስ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

የገበያውን ምስረታ ለማፋጠንም አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን የሚያከናውን የፕሮጀክት ቡድን ተቋቁሟል፡፡ ኤፍኤስዲ አፍሪካ የተባለው ድርጅት የቴክኒክ ድጋፍ፣ ሕጋዊ ጉዳዮችን የማማከር አገልግሎት እና ገበያውን ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ሌሎች ወጭዎችን እንደሚሸፍን በስምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

የኢትዮጵያ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ገበያ ለማቋቋም ሥምምነት ተፈረመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00

XS
SM
MD
LG