በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእርዳታ አቅርቦት በትግራይ


የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ፣ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ
የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ፣ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ

ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ በቅርቡ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በበኩላቸው በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት የሚደረግ የእርዳታ አቅርቦት እየቀጠለ መሆኑን ገልፀው የፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ የእርዳታ እህል እንዲደርሰው የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብለዋል።

ወደ ትግራይ ክልል የገባውን እና እየገባ ያለውን የእርዳታ አቅርቦት በተመለከተ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊዎችን አነጋግረናል።

(የሁለቱንም ኃላፊዎች ምላሽ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

የእርዳታ አቅርቦት በትግራይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:27:42 0:00

XS
SM
MD
LG