በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒውዮርክ በገበያተኞች ላይ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 10 ሰዎች ተገደሉ


ቶፕስ ፍሬንድሊ በተባለው የገበያ ማዕከል ላይ ፣ በጥቂቱ 10 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ተፈጽሟል
ቶፕስ ፍሬንድሊ በተባለው የገበያ ማዕከል ላይ ፣ በጥቂቱ 10 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ተፈጽሟል

በባፋሎ ኒውዮርክ አንድ ታዳጊ ወጣት በአንድ የገበያ ማዕከል ላይ በከፈተው ተኩስ በትንሹ 10 ሰዎችን መግደሉን ፖሊስ አስታወቀ። የጥይት መከላከያ የደረበው እና ባጠለቀው የጦር ባርኔጣ ላይ በተገጠመ ካሜራ ፍጅቱን በቀጥታ ሲያሰራጭ የነበረው ታዳጊ ወጣት ጥቃት ዘርን መሰረት ያደረገ የጽንፈኝነት ጥቃት መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል። ተጨማሪ ሶስት ሰዎችን ያቆሰለው ወጣት እጁን ለጸጥታ ኃይሎች ሰጥቷል ።

የ18 አመቱ ነጭ ወጣት ፣ ቶፕስ በተባለ የገበያ ማዕከል ውስጥ ነበር ጥቃቱን የፈጸመው ።ከጥቃቱ ሰለባዎች መካከል 11 ጥቁሮች ሲሆኑ ሁለቱ ነጮች መሆናቸው ፖሊስ አስታውቋል።የባፍሎ ከተማ ከንቲባ ባይሮን ብራውን ድርጊቱን “አንድ ማህበረሰብ ሊጋፈጠው ከሚችለው ሰቆቃ ሁሉ የከፋ” ብለውታል፣ ከድርጊቱ በኃላ በተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ።

ተጠርጣሪው ጥቃት ፈጻሚ ፔይቶን ጄንደሮን የተባለ ከባፍሎ ከተማ ደቡብ ምስራቅ በኩል 320 ኪሎሜትሮች በምትገኘው ኮንክሊን ነዋሪ መሆኑን ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ ሁለት ህግ አስከባሪዎችን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።በሆስፒታል ታማሚ አልባስ ውስጥ ሆኖ ቅዳሜ ምሽት በመጀመሪያ ደረጃ ግድያ ክስ ወደ ፍርድ ቤት የቀረበው ተጠርጣሪው ካለ ዋስትና በቁጥጥር ስር እንዲቆይ ትዕዛዝ ተላልፎበታል።

XS
SM
MD
LG