በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛኒያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ክፍያ ወለልን ከፍ አደረገች


ሰራተኞች የፊት መሸፈኛ በማዘጋጀት ስራ ላይ ፣ ዳሬሰላም ግንቦት 27 ፥2020
ሰራተኞች የፊት መሸፈኛ በማዘጋጀት ስራ ላይ ፣ ዳሬሰላም ግንቦት 27 ፥2020

የታንዛኒያ ፕሬዚደንት ቅዳሜ ዕለት የሀገሪቱን የሰራተኞች ዝቅተኛ የክፍያ ወለል ለ25 በመቶ በተጠጋ መጠን ማሳደጋቸውን ይፋ አደረጉ። ከእሳቸው በፊት ከነበሩት አንባገነን መሪ ፖሊሲ የተለየ መሆኑ የተነገረለት ውሳኔ በሀገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት የተቀሰቀሱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ የተደረገ ነው።

ፕሬዚደንት ሳምያ ሳሉሁ ሃሰን የክፍያ ወለሉን በ23.3 በመቶ ከማሳደጋቸው በተጨማሪ ከ2016 የአውሮፓዊያኑ ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ ማሳደጋቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል ።

የደሞዝ ጭማሬው የተደረገው የሀገሪቱን ዓመታዊ ጥቅል ምርት ፣ ገቢ እና ዕድገት (በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ) ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መሆኑን ፕሬዚደንቷ አስታውቀዋል ።

የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ጆን ማጋፉሊ ፣ በድንገት በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚደንት ሳልሁ ፣ ከእሳቸው በፊት ከነበሩት መሪ ፖሊሲዎች በተነጠለ መልኩ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ቡድኖች ጋር ተነጋግረዋል። ማጋፉሊ ያለባብሱት የነበረውን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር የተገናኘውን አቀራረብም ቀይረዋል ።

ማጋፉሊ በጥቅምት 2015 ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ፣ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄዎችን ውድቅ በማድረግ ፣ በምትኩ ወደቦችን እና የባቡር ሀዲዶችን መገንባት ፣ የሀገሪቱን ብሄራው አየር መንገድ ማንሰራራት በመሰሉ የመሰረተ ልማት ዘመቻዎች ተጠምደው ታይተዋል

የኮቪድ 19 የጉዞ እግድ ኢኮኖሚያዊ እድገቷ ከ5 መቶ እንዳይሻገር ሳንካ የሆነባት ታንዛኒያ ፣ በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ አሻቅቦባታል ።

የሰራተኞች ቀን በተከበረበት ግንቦት 1 ፣ የሰራተኛ ማህበራት እና ሲቪል ሰራተኞች በመሩት በዶዶማ ከተማ በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ የደሞዝ ጭማሪ ይደረግ ዘንድ ተጠይቋል ።ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው

XS
SM
MD
LG