በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ ጋር የሚያገናኛትን ብቸኛ መተላለፊያ ለፍልስጤማዊያን ሰራተኞች ክፍት አደረገች



ፍልስጤማዊያን ሰራተኞች ወደ እስራኤል ግዛት የሚተላለፉበት የኤሬዝ መተላለፊያ፣ መጋቢት 27 ፣2022 እኤአ የተነሳ
ፍልስጤማዊያን ሰራተኞች ወደ እስራኤል ግዛት የሚተላለፉበት የኤሬዝ መተላለፊያ፣ መጋቢት 27 ፣2022 እኤአ የተነሳ

ከሁለት ሳምንታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ ጋር የሚያገናኛትን ብቸኛ መተላለፊያ ለፍልስጤማዊያን ሰራተኞች ክፍት ማድረጓን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ ።

የፍልስጤማዊያንን ሲቪል ነክ ጉዳይ የሚከታተለው ፣ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ክፍል በምህጻሩ “ኮጋት” ፣ የቀጠናው የደህንነት ሁኔታ ከተገመገመ በኃላ ለሰራተኞች እና የይለፍ ወረቀት ለያዙ ፍልስጤማዊያን የኤሪዝ መተላለፊያ ክፍት እንዲደረግ በዛሬው ዕለት መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

12ሺ ያህል ፍቃድ ያገኙ ፍልስጤማዊያን ሰራተኞች ወደ እስራኤል ገብተው ለመስራት ይሄንን መተላለፊያ ይጠቀማሉ። እስራኤል ከብሄራዊ መታሰቢያ እና ነጻነት ቀኗቿ በፊት ከግንቦት 3 (እኤአ) ጀምራ መተላለፊያን ዘግታ ነበረ። በወቅቱ በጋዛ ሰርጥ ጸጥታ የሰፈነ ቢሆንም ፣ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ በኩል ግን ግጭት ተቀስቅሷል።

እስራኤል እና ሀማስ የተባለው የፍልስጤምን የተጎሳቆለ የባህር ጠረፍ ቀጠና የሚያስተዳድረው የታጠቀ ኃይል ላለፉት 15 ዓመታት ያህል ተፋልመዋል። ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር የተቀሰቀሰው ግጭት የቅርብ ጊዜው መሆኑ ነው።

የእስራኤል ባለስልጣናት የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ቅዱስ የረመዳን ጾም ወር በሆነው ሚያዚያ ወር ግጭት እና ስጋት ያይላል በሚል ሀሳብ ገብቷቸው ነበር። ሌላ ዙር ግጭት በጋዛ ይኖራል ተብሎ ቢሰጋም ፣ የተፈራው ሳይፈጠር ቀርቷል።

በቅርቡ ዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት 2.3 ሚሊየን ፍልስጤማዊያን በሚኖሩበት ጋዛ ያለው የስራ አጥነት መጠን ወደ 48 በመቶ የተጠጋ መሆኑን ይፋ አድርጓል።በእስራኤል ውስጥ ያለው ስራ ለቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ህልውና በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑንም ሪፖርቱ አስረድቷል ።ዘገባው የኤኤፍፒ ነው።

XS
SM
MD
LG