በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጊኒ ወታደራዊ ጁንታ የተቃውሞ ሰልፎችን ከለከለ


የጊኒ ወታደራዊ ጁንታ መሪ ኮረኔል ማማዲ ዱምቦያ
የጊኒ ወታደራዊ ጁንታ መሪ ኮረኔል ማማዲ ዱምቦያ

በአሁን ሰዓት ጊኒን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊ ጁንታ ከሶስት ዓመት በኋላ ስልጣን ለሲቪል መንግስት እንደሚያስረክብ ያስታውቀ ሲሆን ይህን ተከትሎም ማናቸውም ዓይነት ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች በሃገሪቱ እንዳይካሄዱ ከልክሏል።

የሃገሪቱ ብሔራዊ የልማት እና የሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት ኮሚቴ “በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሽግግር እንዳይካሄድ የሚያግዱ እና የኅበረተሰቡን ሰላም የሚያውኩ ሰልፎች የምርጫ ወቅት ደርሶ የቅስቀሳ ዘመቻዎች እስኪጀምሩ ድረስ ታግዷል” ሲል ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫው አክሎም ለሁሉም የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ አንቂዎች ከዚህ እንዲታቀቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህንን መመሪያ መተግበር በማይችሉም ላይ ግን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የምዕራብ አፍሪካ ትብብር ሃገራት ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ጊኒን ከአባልነት አስወጥተዋታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ፣ የቡርኪና ፋሶ፣ ማሊና ጊኒ ወታደራዊ አመራሮች ስልጣን ለሲቪል መሪዎች እንዲያስተላልፉ ጥሪ አድርገዋል

XS
SM
MD
LG