በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን 7 አባል ሃገራት የሩሲያን ‘የስንዴ ጦርነት’ ለማሸነፍ የምጣኔ ሃብት ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል


የቡድን ሰባት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በባልቲክ
የቡድን ሰባት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በባልቲክ

የቡድን ሰባት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬ ዕለት ባደረጉት ስብሰባ ሩሲያ በምጣኔ ሃብት እና በፖለቲካ ገለልተኛ እንድትሆን ለማድረግ ቃል ገቡ።

የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ‘የስንዴ ጦርነት’ ሲሉ የጠሩት እና በሩሲያ የተደቀነባቸውን ጦርነት ለማሸነፍ አባል ሃገራቱ ለዩክሬን እየደረጉ ያሉትን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሰፊው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በባልቲክ ባህር ላይ በሚገኝ መዛዝኛ የተገናኙት የብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ሕብረት አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ የመሳሪያ ልገሳው እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በተጨማሪም የሩሲያን ምጣኔ ሃብት ለመጉዳት እና ፑቲን በምርጫው የገባበትን ጦርነት ለማስቆም በሩሲያ ባለሃብቶች ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉም አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ሕብረት የውጪ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ “የተኩስ አቁም ለማድረግ ምንም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ተነሳሽነት የለም” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ብላድሚር ፑቲን ለሁሉም ሰው ጦርነቱን ማቆም አልሻም ብሏል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG