በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ፖሊሶች በአልጄዚራዋ ጋዜጠኛ ቀብር ስነስርዓት ላይ የፈጸሙት ድብደባ ተወገዘ


የአልጄዚራ ጋዜጠኛዋ የቀብር ስነስርዓት ላይ የእስራኤል ፖሊሶች ለቀስተኞቹ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ
የአልጄዚራ ጋዜጠኛዋ የቀብር ስነስርዓት ላይ የእስራኤል ፖሊሶች ለቀስተኞቹ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ

ፍልስጤም አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አክሌህ አስክሬንን ተሸክመው ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ድብደባ ባደረሱ የእስራኤል ፖሊሶች ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ ተቃውሞ አደረጉ። የእስራኤል ፖሊሶች ባደረጉት ድብደባ የጋዜጠኛዋ አስክሬን ሊወድቅ ነበር።

ታዋቂዋ የአልጄዚራ ጋዜጠኛ በዌስት ባንክ ከተገደለች ከሁለት ቀናት ትላንት አርብ በቀብር ስነስርዓቷ ላይ ለመታደም እጅግ በዙ ሰዎች በእየሩሳሌም ጥንታዊው ከተማ ተግኝተዋል።

በቴሌቪዥን የተላለፉ ምስሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የእስራኤል ፖሊሶች የፍልስጤም ባንዲራ ከያዙ ለቀስተኞች ላይ ለመቀማት ሲሞክሩ እና አስክሬኑን የተሸከሙ ሰዎችን በቆመጥ ሲመቱ የታየ ሲሆን በዚህ የተነሳም የአስክሬን ሳጥኑ ከእጃቸው አምልጦ ሊወድቅ ሲል ታይቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታውን ‘እጅግ የሚረብሽ’ ስትል የአውሮፓ ሕብረት ደግሞ ፖሊሶቹ በተጠቀሙት ‘አላስፈላጊ ጉልበት ተደናግጫለሁ’ ብሏል።

በሁኔታው በቦታው የነበሩ 33 ሰዎች ሲጎዱ ሌሎች ስድስት ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል መግባታቸውን የእየሩሳሌም ቀይ ጨረቃ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG